Yiqochegnal Lyrics
- Genre:World Music/Folklore
- Year of Release:2023
Lyrics
ይቆጨኛል
የሚያስደንቅ ፍቅር አልነበረ ዎይ ቤታችን
ምን ይሆን የገባዉ ይህን ሰሞን መሀላችን
ያየን ሁሉ ትላንት የቀናብን
ሲያልቅ አያምር ብሎ ተረተብን
መቼም የማይሰማው የለ ጆሮ
ወሬዉ ያደርሰኛል ዞሮ ዞሮ
ይቆጨኛል ይነደኛል
ልክ እንደሳት ይፈጀኛል
እኔ ካንቺ በቀር አልፈልግም ሌላ
ቆንጆ ቢትረፈረፍ ሀገሩን ቢሞላ
የማፍቀሬን መጠን ቃል አይገልፅልኝም
እዉነቱን ስነግርሽ ለምን አታምኚኝም
የወቶሮ ሳቅና ጨዋታሽን
እንጂ ምፈልገዉ ፈገግታሽን
ሲከፋሽ አልወደም ይጨንቀኛል
ስታኮርፊ ሰላም ይርቀኛል
ኧረ እንዴት ላድርገዉ ታዲያ ኧረ እንዴት
ሂወቴን እንዳልገፋዉ በንዴት
አዝማች
የትላንቱ ፍቅር ዳግም እንዲመለስ
ቁጭ ብለን እናዉጋ በሰከነ መንፈስ
ለጋራ ኑሮአችን ስንል እንግባባ
ተይ አንጨቃጨቅ በነጋ በጠባ
ባላይም ሰማለሁ ባፍ ሲወራ
እቃም እንደሚጋጭ ከእቃ ጋራ
ታዲያ ለምንድንነው የኛን ችግር
እኛዉ የማንፈታዉ በንግግር
ኧረ እንዴት ላድርገዉ ታዲያ ኧረ እንዴት
ሂወቴን እንዳልገፋዉ በንዴት
ይቆጨኛል ይነደኛል
ልክ እንደሳት ይፈጀኛል