Loading...

Download
  • Genre:Reggae
  • Year of Release:2021

Lyrics

የመውጫ ሃሳብ


የመውጫ ሀሳብ

ከጊዜ ህግግጋት ውጭ የሆነው ፈጣሪ

እንደወንዝ የተነጠፈውን የሰው ልጅን ትውልድ ከመጀሪያው አንስቶ እስከጨረሻው ይመለከታል

የሆነውን ያውቃል ሚሆነውን ያውቃል

እኔም ሀሳቤ የሶስት ዘመን ሰው ላይ አረፈ

የኔን የሶስተኛ ዘመንን ሰው ግን እጅጉን ፈራሁት

ሚሆነውን እሱ ያውቃል


አንደኛው የዘመን ሰው

የመቶ አመት ታላቄ የኋለኛው

ባዶ እግሩን ሀገሩን ያቀናው

በላብ በደሙ የመሬቱን ድንበር የሳለው

ባምላኩ ፍቃድ የሚኖረው

በፆም በፀሎቱ ሰማይን ሚቀደው

ጤና ይስጥልኝ ይላል ወዳጁን ሲያገኘው

መልካሙን ብቻ ነው የሚመኘው

የሰው ስሜትን ነው የለበሰው


ደሙ ትኩስ ለጠላቱ

ሀገር ይጨሳል ሲቆጣ ስሜቱ

አይኑ ፈጦ ባፍሮ ፀጉሩ

አንበሳን መስሎ ከነምንሽሩ

ውስጡ ደግሞ አለ ትህትና

ዛሬን የሚያስንቅ ዛሬን የሚያስቀና

ቤቴማ የግዜር ነው ብሎ

መኝታን ለቆ ከመደብ ያድራል መሬት ወድቆ


የሰው ልክ የሰው መልካም

ስብእናው አይለካም

እሱን መስሎ እራሱን ቀርፆ ባህሪውን ስሎ

ከወገኑ ከሚወደው እንደወጉ እንደቀየው

ሳይማረጥ ዘር ሳይቆጥር ኖረ ተቻችሎ

ያባት አባት ያገር አድባር ያዛውንቱን ፍቅራቸውን

ምርቃቱን በረከቱን ምክሩና ተቀብሎ

ፈጣሪውን አከበረ በሰው ልጅ ላይ እየቆጠረ

የሰማዩን በምድር ሊፈታ ሰው ባማላኩ ብሎ

ግን ዛሬ በህይወት የለም ካፈር በታች ውሎ


የሶስት ዘመን ሰው…

ቅድም አያቴ….እኔ…….የልጅ ልጄ


ሁለተኛው እኔ ነኝ

የዚህ ዘመን ነኝ

ካንደኛው የተመዘዝኩ

ግን የተለወጥኩ

መልሼ እራሱን የምወቅሰው

ታሪኩን የማራክሰው

ኃላ ቀር ነው እለዋለሁ

ምን ተውክልኝ እለዋለሁ

ሰውነቱን አረክሳለሁ

የሰራውን አፈርሳለሁ

ካፈሩ በታች ገብቼ

ሰላም እረፍቱን ነስቼ

በነገር ቢላ ስጠቀጥቀው

እሱ ግን አያወጋኝም ሄዷል

መልስም የለው

እሱ ግን መልስም የለው


ከወንድሜ ጋር ሰላም የለኝ

መንገዴ ሁሉ የጠፋብኝ

ቴክኖሎጂ የበዛብኝ

ብቸኝነት የሚያጠቃኝ

ትልቅ ሀገር ተረክቤ

ትንሽ ሆኜ ጠቦ ሀሳቤ

ከፋፍዬ አሳነስኳት

መላወሻም አሳጣኋት

የኔ ስልጣኔ ሆነ መጥኔ


የሶስት ዘመን ሰው…

ቅድም አያቴ….እኔ…….የልጅ ልጄ


የሶስተኛ ዘመንን ሰው ፈራሁት

የሶስተኛ ዘመንን ሰው ፈራሁት

የሶስተኛ ዘመንን ሰው ፈራሁት


ታሪኬን ሁሉ እየበረበረ

የተፃፈውን እየመነዘረ

ሀገር እንደቀማሁት ሲያውቅ ደነገጠ

ንዴቱ ሁሉ ምድርን አግሎ አቀለጠ

በጣም ጨሶ እርር ብሎ እሳት እያናፋ

ገላ አጥንትን የሚሰብር ቃላት እየተፋ

ከምድር በታች ሙት ወድቄ አፈር ቢጫነኝም

ያረኩትን አውቃለሁና እረፍትስ የለኝም


ሀገር የለው ወገን የለው ከሜዳ በትኜው

አረኩት ሆደ ባሻ ታሪኩን አጥፍቼው

ከኔ የባሰ አውሬነቱ ከውስጡ ቢወጣ

ጥፋቱ ማይመዘን ሀዘኑ ቅጥ አጣ


ሀዘኑ ቅጥ አጣ….ምን ያደርገው ታዲያ ….. ሀገሩን ቀምቼው

ሀገሩን ቀምቼው

+

      -   or   -

      -   or   -

      NG +234

          Please Select A Playlist

          Add New Playlist

          Share on

          Embed: Love & Light EP

          Custom Size :

          • Default
          • Desktop(300*600)
          • Mobile(300*250)

          Type :

          • HTML/HTML5 (WordPress Supported)
          Get Boomplay Premium
          for
          Payment Method
          Pay With
            Review and pay
            Order Date
            Payment Method
            Due Today
            Flutterwave
              Subscription Successful

              Congratulations! You have successfully activated Boomplay 1 Month Premium.

              Now you have access to all the features of Boomplay App.
              Payment Failed

              Please check your balance and then try again.

              You'll lose your subscription if we don't have a working payment method for your account, so please check your payment details.
              Need help? Contact Boomplay Subscription Support.
              Payment Processing...
              10 s

              Payment is being processed by . Please wait while the order is being comfirmed.

              Payment Processing
              Your order is processing, and it may take up to a few days for the service provider to handle your payment. Please kindly stay tuned and check your order status in ‘User Center’.
              About Order Status