Meteche Neber Lyrics
- Genre:Afrobeats
- Year of Release:2024
Lyrics
Meteche Neber - Mastewal Eyayu
...
መጥቼ ነበር ቤትሽም
አለሁኝ ብለሽ የለሽም
ሳጣሽ ያጣሁት ምኔን ነው
አንቺን አይደለም እኔን ነው
ጉንጭ አያወጣም ሰምበር
አይጎልም ቢሳም ከንፈር
አቅፈው የላኩት ዳብሰው
ከአካል ምልክት አይተው
የለሽም እንደቀላል ተራ ድክመት
የለሽም እንዳላየው ያንቺን ስህተት
የለሽም ልቀበልሽ ብልስ ንቄ
ሄደሽስ ያረግሽውን ምን አውቄ
በምን ያስታውቃል ሰው የዋለበት
ሄደው ሲያጡት እንጂ አለሁ ካለበት
የለሽም ከቦታው ካየሁሽ ከፍታ
ውለሻል ከጤዛው ከውሀ ጠብታ
የለሽም ከቦታው ካየሁሽ ከፍታ
ሆነሻል የጤዛው የውሀ ጠብታ
መጥቼ ነበር ቤትሽም
አለሁኝ ብለሽ የለሽም
ሳጣሽ ያጣሁት ምኔን ነው
አንቺን አይደለም እኔን ነው
ጉንጭ አያወጣም ሰምበር
አይጎልም ቢሳም ከንፈር
አቅፈው የላኩት ነክተው
ከአካል ምልክት አይተው
ባየሽኝ በምሽቱ በረድ መኻል
ባየሽኝ ተሸክሜ በድን አካል
ባየሽኝ አንቺን ሳጣሽ እምነት ክብሬን
ባየሽኝ ላልል ቀና መሰበሬን
በነፍስ የተሞላ አካል እንዳልነበር
ላይን ይጠወልጋል ሰው ልቡ ሲሰበር
የለሽም ከቦታው ካየሁሽ ከፍታ
ውለሻል ከጤዛው ከውሀ ጠብታው
የለሽም ከቦታው ካየሁሽ ከፍታ
ሆነሻል የጤዛው የውሀ ጠብታ
መጥቼ ነበር ቤትሽም
አለሁኝ ብለሽ የለሽም